በአፍሪካ የተፈናቃዮች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል - ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት በቦራም ካውንቲ፣ ደቡብ ኮርዶፋን፣ ሱዳን ውስጥ በሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ምግብ ለማግኘት እየተጠባበቁ፤ እአአ ሰኔ 22/2024

Your browser doesn’t support HTML5

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

በአፍሪካ የተፈናቃዮች ሰዎች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩን እና 35 ሚሊዮን መድረሱን ዓለም አቀፉ የሀገር ውስጥ ተናቃዮች ተከታታይ ማዕከል ይፋ ያደረገው ዐዲስ ሪፖርት አመለከተ። ከእነዚህም ውስጥ ቁጥራቸው 32.5 ሚሊዮን የሚደርሱት በግጭት እና ሁከት ሳቢያ ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ ናቸው።

ትላንት ማክሰኞ የታተመው ሪፖርት አያይዞም፤ በአህጉሪቱ ያለውን በሃገር ውስጥ የመፈናቀል ፈተና ለመፍታት መንግሥታት የሚያደርጉትን ጥረት የሚበረታታ ቢሆንም፤ ‘በቂ አይደለም’ ብሏል።

መሀመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያደረሰን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።