Your browser doesn’t support HTML5
በምግብ ዋስትና ላይ የሚወያይ የአፍሪካ የግብርና ሚንስትሮች ጉባዔ በካምፓላ
የአፍሪካ ሀገሮች የግብርና ሚንስትሮች በዚህ ሳምንት ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ላይ ጉባኤ ላይ ናቸው። የተሰበሰቡት የአህጉሪቱን የምግብ አመራረት ሥርዐቶች ለማሻሻል ስለሚቻልበት መንገድ ለመምከር ነው። ሚንስትሮቹ አፍሪካ ከውጭ በሚገባ ምግብ ላይ መተማመኗን ለመቀነስ ብሎም የአሕጉሪቱን አስተራረስ ከአየር ንብረት ለውጡ እና ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋራ በሚጣጣም መንገድ ለማሻሻል በታለመው የዐስር ዓመት ዕቅድ ከስምምነት ለመድረስ ተስፋ ማድረጋቸውን ጠቅሶ መሐመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።