አፍጋኒስታን በምትገኘው ሄልማንድ ክፍለ-ሃገር ላይ የተካሄደ የውጭ የአየር ድብደባ በሥህተት ቢያንስ 17 የመንግሥት ወታደሮችን ገድሎ 14 አቁስሏል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የፀጥታ ባለሥልጣን በተናግረው መሰረት የአየር ድብበደባው የተካሄደው ከክፍለ-ሀገሩ መዲና ላሽካር ጋህ ወጣ ብሎ በሚገኝ የፖሊስ ኃይሎች ከታሊባን አማፅያን ጋር ይዋጉ በነበረበት ቦታ ላይ ነው።
አተሁላህ አፍጋን የተባሉ ሄልማንድ ያለው የክፍለ-ሀገሩ ምክር ቤት ኃላፊ የአውራ-ጎዳና የፖሊስ ግብረ-ኃይል አዛዥ በስህተት ከተገደሉት መካከል አንዱ መሆናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።