አፍጋኒስታን ውስጥ በደረሰ ጥቃት 6 የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮች ወታደሮች ተገደሉ

አፍጋኒስታን ውስጥ አንድ ሞተር ቢስኪሊት የሚነዳ አጥፍቶ ጠፊ ባግራም የአየሮፕላን ማረፍያ አጠገብ በነበረ የዩናትድ ስቴትስ (United States) እና የፍጋኒስታን የጣምራ ጥበቃ ቦታ ላይ ባደረሰው ጥቃት 6 የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮች ድርጅት ወታደሮች እንደተገደሉ ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉ NATO አረጋግጧል።

ባግራም ወያደራዊ አየሮፕላን ማረፍያ አፍጋኒስታን ውስጥ ከሚገኙት ወታዳራዊው ሰፈሮች ትልቁ እንደሆነና በደረሰው ጥቃት ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የ (NATO) ቃል አቀባይ ማይክል ላውሆርን (Michael Lawhorn) ገልጸዋል። የዜና ዘገባ አለን ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አፍጋኒስታን ውስጥ በደረሰ ጥቃት 6 የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮች ወታደሮች ተገደሉ