በአፍጋን ለተመታው አብራሪ ሃሊፊነት የወሰድ አካል የለም

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል

በደቡባዊ አፍጋኒስታን ካንዳሃር በተባለች አካባቢ አንድ የአየር ሃይል አብራሪ ተመታ። ፖሊስ አንድ የወታደራዊ ሃይል አባል መገደሉን ለቪኦኤ አረጋግጦ ዝርዝር ከመናገር ተቆጥቧል።

ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉት የደህንነት አባሉ ለቪኦኤ እንዳረጋገጡት የወታደራዊ ሄሊኮፕተር አብራሪው ማሱድ አታል በአገሪቱ ገዢ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰ መሳሪያ ተገድሏል።

አታል የካንዳር አካባቢ ነዋሪ የነበረና በቼዝ ሪፐብሊክ እና በየተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሰለጠነ አብራሪነበር። እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

በአፍጋኒስታን የመብት ተሟጋቾች እና የጋዜጠኞች ግድያ የጨመረ ሲሆን ባለፈው ሁለት ወራት ውስጥ አምስት ጋዜጠኞች ተግደለዋል። ትናንት ማክሰኞ መግለጫ የሰጡት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐመድ አንዳራቢ የታሊባን ቡድን የሚያደርሰው ጥቃት እየጨመረ ነው ብለዋል።