አጥፍቶ ጠፊ አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ ባደረሰው ጥቃት 12 ሰዎች ሞተው ሌሎች ከ30 በላይ መቁሰላቸው ተገለፀ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
አጥፍቶ ጠፊ አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ ባደረሰው ጥቃት 12 ሰዎች ሞተው ሌሎች ከ30 በላይ መቁሰላቸው ተገለፀ።
የዛሬው ጥቃት የደረሰው፣ የመንግሥቱ ኃይሎች አፍጋኒስታን አካባቢ በታሊባን ላይ የጀመሩትን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ማቆማቸውን ባስታወቁ ማግሥት መሆኑም ታውቋል።
የአፍጋኒስታን ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ ጥቃቱ የደረሰው፣ ዋና ከተማዋ ውስጥ በሚገኘው የከተማ ልማትና መልሶ ማቋቋም መሥሪያ ቤት መግቢያ ላይ ነው። ከሠለባዎቹ መካከል የሚኒስቴሩ አባላትም እንደሚገኙባቸው ተገልጧል።
ለዚህ ጥቃት እስላማዊ መንሥግት ነኝ ባዩ አማፂ ቡድን ኃላፊነት መውሰዱን አስታውቋል።