በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ የደረሰው ርእደ መሬት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ አስከተለ

ፎቶ ፋይል፦ ሰመራ፣ አፋር

Your browser doesn’t support HTML5

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ   የደረሰው ርእደ መሬት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ አስከተለ

በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ደጋግሞ የደረሰው ርዕደ መሬት በት/ቤቶች ላይ ጉዳት በማድረሱ ከ600 በላይ ተማሪዎች ዛፍ ጥላ ስር ለመማር መገደዳቸውን የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በርዕደ መሬቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ት/ቤቶች ውስጥ በዋናነት በሚጠቀሱት የሳቡሬ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የደረሰው ቁሳዊ ጉዳት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽእኖ ከማሳደሩ ባሻገር በመቶዎች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥ ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/