የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት መግለጫ

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንንና አፋር ክልልን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች በሚፈጠሩ ግጭቶች የሚጠፋው ህይወትና የሚደርሰው ጉዳይ እያሳሰበው እንደሆነ የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት አስታውቋል።

“ደም አፋሳሽ ግጭቶች እንዳይደገሙ መንግሥት የህግ የበላይነትን ያስከብር” ብሏል ድርጅቱ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው መግለጫ።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደግሞ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክቷል።

ይሁን እንጅ ጥቃቶቹ የሚፈፀሙት በደፈጣ ከመሆኑ ባሻገር ኅብረተሰቡም አጥፊዎችን አሳልፎ የመስጠት ልማድ አለማዳበሩና የመንግሥት አካላትም በሚጠበቅባቸው ልክ አለመንቀሳቀሳቸው መፍትኄ ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት እንዳከበደው የዞኑ አስተዳደር ጠቁሟል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት መግለጫ