‘በደቡብ ግፍ እየተፈፀመ ነው’ ሲል መኢአድ አቤት አለ

በደቡብ ክልል በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ነው ያለውን ግፍ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያስቆም መኢአድ ጠየቀ። በክልሉ አባሎቹ በህገ ወጥ መንገድ እየታሠሩ መሆናቸውንም መኢአድ ገልጿል፡፡

የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ባለፈው ሣምንት መጨረሻ በፅሁፍ ባሠራጨው መግለጫ በደቡብ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር ውስጥ እጅግ የከፋ ኢሰብዓዊና ኢዴሞክራሲያዊ ድርጊት በዜጎች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ዘግቧል፡፡

በቤንች ማጂ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ በ223 አባወራዎች ላይ አፈሣ መፈፀሙንና 56 ሰዎች መታሠራቸውን የጠቆመው ይኸው መግለጫ እነዚህ አባወራዎች ለዓመታት ከኖሩበት መንደር መፈናቀል ምክንያት የሆነው የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር የሰጡት ትዕዛዝ ነው፡፡

አቶ ሺፈራው ሽጉጤ የፈረሙት የትዕዛዝ ሠነድ “… በተለይ ከሰሜን የአማራው ክልል የመጡ …” የሚል ሃረግ እንደሚገኝበት የመኢአድ ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊ አቶ ጌታቸው አበበ ገልፀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከመለስካቸው አመሃ ዘገባ ያዳምጡ።