ብሔራዊው ቅርስ የጉለሌው ሼኽ ኦጀሌ ቤተ መንግሥት በመፍረስ አፋፍ ላይ ነው

  • መለስካቸው አምሃ

Your browser doesn’t support HTML5

ብሔራዊው ቅርስ የጉለሌው ሼኽ ኦጀሌ ቤተ መንግሥት በመፍረስ አፋፍ ላይ ነው

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እና እንደ ሀገረ መንግሥት ካላት ረዥም ታሪክ አኳያ፣ ብዙ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ የቅርስ ሀብት እንዳላት የታወቀ ነው፡፡

ከእኒኽም ጥቂቶቹን፣ ከብሔራዊ ጸጋነት ባሻገር በዓለም የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶች ማኅደር ውስጥ፣ የሰው ልጆች ኹሉ ሀብት እንዲኾኑ አስመዝግባለች፡፡

አንዳንዶቹ ደግሞ፣ የቅርስነት ዕሴታቸው እጅግ ከፍ ያለ ቢኾንም፣ በቂ እንክብካቤ አላገኙም፡፡ ሌሎቹም፣ ጭራሹን እንዲጠፉ የተተዉ እስኪመስል ድረስ፣ እንደ ውዳቂ ዕቃ ተረስተዋል፡፡

በዐዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የሼኽ ኦጄሌ አል ሐሰን መኖሪያ የነበረው ግዙፍ ሕንፃ፣ “ለውድመት የተጋለጡ” ከሚባሉ ብሔራዊ ቅርሶች አንዱ ነው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።