ለዐዲስ አበባ የትውልዶች ፈተና ለኾነው የቤት ዕጦት የመሬት ፖሊሲ ማሻሻያ ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያስገኝ ተጠቆመ

Your browser doesn’t support HTML5

ለዐዲስ አበባ የትውልዶች ፈተና ለኾነው የቤት ዕጦት የመሬት ፖሊሲ ማሻሻያ ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያስገኝ ተጠቆመ

በከተሞች የሚታየውን የመኖርያ ቤት እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት፣ የመሬት ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ እንደሚያስፈልግ፣ የከተማ ዕቅድ ባለሞያው እና የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ አርክቴክት ዮሐንስ መኰንን ገለጹ፡፡

የዐዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የጋራ መኖርያ ቤት ዕጦት እና የተጋነነ ኪራይ እየፈተናቸው እንደኾነ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የአሜሪካ ድምፅ፣ የከተማ አስተዳደሩን ምላሽ ለማካተት ያደረገው ጥረት ባይሳካም፣ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ዐዲስ አማራጮችን እየተገበረ እንደኾነ፣ ከንቲባዋ ከዚኽ ቀደም አስታውቀው ነበር፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።