በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሠራተኞች የደመወዝ ወለል ሳይወጣ፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ያሳለፈው ውሳኔ አነጋጋሪ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም ፈደሬሽን፣ “የገቢዎች ቢሮው ያሳለፈው ውሳኔ የኢንዱስትሪ ሰላምን እንዳያውክ እሰጋለኹ” ብሏል።
Your browser doesn’t support HTML5
የፌደሬሽኑ ፕሬዝደንት ዶ.ር. ፍትህ ወልደሰንበት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ቢሮው ይፋ ያደረገው፣ የንግድ ተቋማት ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን፣ የንግድ ሥራ በነፃነት እንዳይከናወን ያደርጋል ይላሉ። በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡ የሕግ ባለሞያ ደግሞ፣ የገቢዎች ቢሮው እንዲህ ዓይነት ውሳኔ የማሳለፍ ስሥጣን የለውም ካሉ በኋላ፣ ጉዳዩ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄን ሊያስነሳ እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበኩሉ፣ “የግብር ስወራን ለመከላከል የሚያስችል የአሠራር ስርዐት ነው የዘረጋኹት፣ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አይደለም” ብሏል።