ለሀገርና ለህዝብ ሥጋት የተባሉ ተቋማት

አዲስ አበባ

አንዳንድ ድርጅቶች ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ለሀገር እና ለህዝብ ስጋት የሆነ ተግባር ላይ መሰማራታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ባለፉት 15 ቀናት የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ287 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል።

የፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃለ አቀባይ አቶ ጀይላን አብዲ ለአሜሪካ ድምፅ እንደ ገለፁት የአጥፊ ቡድኑ ህገወጥ መሳሪያዎችን በየመንገዱ መጣል ጀምሯል።

ህብረተሰቡ በንቃት እራሱን እና አካባቢውን መጠበቅ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

Your browser doesn’t support HTML5

ለሀገርና ለህዝብ ሥጋት የተባሉ ተቋማት