Your browser doesn’t support HTML5
አዲሷ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ኢሶዴፓ መሪ ዶር. ራሔል ባፌ፣ የፓርቲው ሊቀ መንበር የነበሩትን የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ፈር ተከትለው፣ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልን እንደሚያስቀጥሉ ተናገሩ፡፡ ፓርቲያቸው፣ እሳቸውን በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ምትክ፣ መሪ አድርጎ እንደሾማቸውም ገልፀዋል፡፡ በኢትዮጵያ ስላለው የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው መምህር ዶር. ዮናስ አሽኔ በበኩላቸው፣ ዶር. ራሔል ባፌ የሚመሩትን የኢሶዴፓ ፓርቲን ጨምሮ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩ ልዩ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንዳሉባቸው ገልፀዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴ እንዲያደርጉም፣ የጋራ ጥምረት መፍጠር እንዳለባቸው መክረዋል፡፡