የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ያበቃውን ሥልጣናቸውን በሕገወጥ መንገድ ለማራዘም ጥረት እያደረጉ ነው ሲሉ አምስት ፓርቲዎች አቤቱታ አቀረቡ
ምርጫ ቦርድ፣ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቶ የጋራ ምክር ቤቱን የሚመሩ አመራሮችን እንዲያስመርጥም ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል፡፡
ከበርካታ አባል ፓርቲዎች ውስጥ አቤቱታውን ያቀረቡት አምስት ብቻ መሆናቸውን የጠቀሱት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ በበኩላቸው፣ “የሥራ አስፈጻሚ አባላት ሥልጣናቸውን ለማራዘም ያደረጉት ጥረትም ሆነ ፍላጎት የለም” ብለዋል፡፡
ምክር ቤቱ ጉባኤ ለማካሔድ በዝግጅት ላይ እንደሆነ እና እስካሁን ያልተጠራው ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ቀውስ አንጻር የሥራ ጫናዎች በመብዛታቸው ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ ሌሎች ፓርቲዎች ያላቸውን አቋም ለማረጋገጥ አልቻለም፡፡