የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ተከበረ

Your browser doesn’t support HTML5

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ተከበረ

ዓመታዊው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ከተለያዩ የሀገርቱ ክፍሎች የመጡ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እንደዚሁም ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እና የውጭ አገራት ዜጎች በተገኙበት ዛሬ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ/ም በደማቅ ሥነ ስርዓት ተከብሯል።

ዛሬ ማለዳ በመስቀል አደባባይ አካባቢ ባለዉ የኢሬቻ ቦታ በተከበረው በዓል ላይ የተገኙ ታዳሚዎች ወደ ከተማዋ የገቡት ከትላንት ከሰዓት አንስተዉ ነው። ኢሬቻ አሁን የብዙ ህዝቦች መገናኛ ቦታ እየሆነ ነው ሲሉ ተሳታፊዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።