Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ሁኔታ አሳሳቢ ኾኖ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።
በአዲስ አበባ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተወስደው ያሉበት ሳይታወቅ፣ መደበኛ ባልሆነ ቦታ እንዲቆዩ ተደርገዋል ያሉ ሰዎችን በተመለከተ ዛሬ ሪፖርት ያወጣው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ፣ 52 ሰዎችን የተመለከቱ አቤቱታዎችን መመርመሩን አስታውቋል።
ከእነዚኽ ውስጥ 44 ሰዎች ከአንድ እስከ ዘጠኝ ወር ድረስ፣ በተለያዩ መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸውን አመልክቷል።
እስካሁን ያሉበት ከማይታወቁ ግለሰቦች መካከል የአንዱ ባለቤት ለአሜሪካ ድምጽ በሰጠችው አስተያየት፣ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ለስድስት ወራት ባለቤቷን ለማፈላለግ ብትሞክርም ያለበትን ማወቅ እንዳልቻለች ተናግራለች። ከሁለት ልጆቿ ጋራ ለችግር በመጋለጧ ቤተሰቦቿን ተጠግታ መኖር መጀመሯንም ገልጻለች።
በአስገዳጅ ሁኔታ ተይዘው ያሉበት ሳይታወቅ ቆይተው ከተለቀቁት ሰዎች መካከል ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁ ስለመኖራቸው የተናገሩት የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ሥራ ክፍል የሪጅን ዳይሬክተር ሰላማዊት ግርማይ፣ ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑ መንግሥት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።