የአዲስ አበባ ከተማ የድህነቷ መገለጫ ከሆኑት አንዱ በሆነ የመኖሪያና የንግድ ሠፈር የሚተኙበትን አልጋ የሚያከራዩ ሰዎች አሉ፡፡
በተለምዶ ጎጃም በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቀበሌ 32 ግራና ቀኙን የተፋፈጉ መኖሪያ ቤቶችን እየተመለከተ ላይና ታች የሚሄድ ሁሉ የሚያውቃት ወጣት ዛሬም እዚያው አለች፡፡
ዕድሜዋ በሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ የሆነ ወጣት ወጥት ነፍስ ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ሌሊቱ አሥር ሰዓት ድረስ ይኸው መንገድ ዳር ናት፡፡
“አልጋ አለ፤ ቆንጆ አልጋ…” እያለች ትጣራለች፡፡
ወጣቷ ተከራዮቹን ውስጥ ውስጡን ይዛ ሄዳ እናት አባቷ ቤት ታደርሣለች፡፡ ወላጆቿ ካፈሯቸው ስድስት ልጆች አራተኛ የሆነችው ይህቺ ወጣት እንደምትለው የወላጆቿ ቤት አንድ ክፍል ብቻ ነው፡፡
የሚያከራይዋቸው ማደሪያዎች ያሉት በዚህ አንድ ክፍል ላይ በተሠራው ቆጥ ላይ ነው፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡
(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)