ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ በአዲስ አበባ የተገደሉትና መንግሥት “ጽንፈኛ” እያለ የሚጠራው የፋኖ አመራሮች ሁለት የቤተሰብ አባላት መታሰራቸውን፣ የአሜሪካ ድምፅ ምንጮች አስታወቁ፡፡
ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን አንድ የሟቾቹ የቤተሰብ አባል፣ አስከሬን ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያመሩ ሁለት የቤተሰብ አባላት ተይዘው መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡ የሟቾቹ ወላጅ እናቶችም እስከ አሁን አስከሬን መውሰድ እንዳልቻሉ ግለሰቡ ጠቁመዋል፡፡
ስለ ጉዳዩ፣ ከአዲስ አበባ እና ከፌደራል ፖሊስ ተቋማት አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።