ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ሰሞኑን በተስተዋለው ሁከት ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዚሁ መልዕክታቸው የደረሱ ጥፋቶችን ዘርዝረው እንኳን ለማየት ለመስማት የሚዘገንን ዕኩይ ተግባር በወገናችን ላይ ተፈፅሟል ብለዋል።
የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና አጥፊዎች በህግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ሁሉ እንዲያገኙ ያለማወላወል እንሰራለን ብለዋል።
ጠ/ሚሩ ዶ/ር ዐብይ አህመድ አክለው ፈታኞቻችን ያልተገነዘቡት ነገር ቢኖር የተከፈለውን መስዕዋትነት ከፍለን የኢትዮጵያንና የህዝቦቿ ብልፅግና የምናረጋግጥ መሆናችንን እንገልፃለን ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ ለርስ በርስ መተማመን ምንም ዓይነት ጥያቄ ቅሬታና ተቃውሞ ቢኖር በሰለጠነና ምንም ዓይነት ጥፋት በማያደርስ መልኩ ህግን ተከትሎ ማቅረብን ባህላችን እናድርግ ሲሉ ሊቀ ጳጳሳት ዘ ካቶሊካውያንና የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል ጥሪ አሰምተዋል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5