ጠ/ሚ ዐብይ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ - ክፍል አንድ

  • እስክንድር ፍሬው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ

የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት “ልንወረወርበት ከነበረው አዘቅት የማገገም ሁኔታ አሣይቷል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በተለይ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ መንበረ ሥልጣኑ ከመዝለቃቸው በፊት ከነበረው ጊዜ ጋር የአሁን ሁኔታዎችን ማነፃፀር አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ቢጠቁሙም አሁን ግን የሰላም አየርና የእፎይታ መንፈስ እንዳለ አመልክተዋል።

ፍላጎት ዘወትር የማይቆም መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰው በዚያው መጠን ጥረትና ሥራውም እንዲያድግ ለማድረግ እንደሚሠሩ፤ ተጨብጧል ያሉት መልካም ነገር ሁሉ እንዲሠፋና ሁሉንም እንዲነካ ለማድረግ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

እርሣቸው ወደ መንበረ ሥልጣኑ የዘለቁበት ጊዜ ሃገሪቱ የነበረችበት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ እንደምን ተስፋ እንዳላስቆረጣቸውና ተስፋቸውስ ከየት እንደመጣ የተጠየቁት ዶ/ር ዐብይ በፈጣሪ፣ በሃገሬና በሕዝቤ ምንጊዜም ተስፋ አልቆርጥም ብለዋል።

“የኢትዮጵያ አምላክ የዘገየ ቢመስልም ይቀራል ብዬ አላምንም፤ ኢትዮጵያንም ይተዋል ብዬ አላምንም፤ ኢትዮጵያዊያን በሃገራቸው ተስፋ አይቆርጡም፤ ውጭ ያሉት እንኳ እንቅልፋቸው አሜሪካ፣ ሕልማቸው ኢትዮጵያ ነው” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒትስስስትሩ አክለውም ውጭ በሄዱ ጊዜ ሁሉ የሚያዩትን ውበትና መልካም ነገር ሁሉ እንደምን በሃገራቸው ያንን ማድረግ እንደሚቻል ዘወትር እንደሚያስቡና እንደሚጨነቁ አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቪኦኤ ጋር በተለይ ያደረጉት ቃለ-ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ጠ/ሚ ዐብይ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ - ክፍል አንድ