Your browser doesn’t support HTML5
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ላለፉት 30 አመታት ሲያስተምረው የነበረውን፣ የትግርኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማቋረጥ ያሳለፈው ውሳኔ ትክክል አይደለም ሲሉ ባለሙያዎች ተቃወሙ፡፡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ የዩኒቨርሲቲው ውሳኔ፣ በትግራይ ባህል፣ ቋንቋ እና ስነቃል ዙርያ ሲደረጉ የነበሩትን የምርምር ስራዎች ያጎድላል በማለት ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ የራስገዝ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋም ከመሆኑ ጋራ ተያይዞ፣ የፕሮግራሞች ክለሳ ማድረጉን ገልፆ፣ አሳታፊ ባለው የዳሰሳ ጥናት ላይ ተመስርቶ 14 ፕሮግራሞች እንዲቋረጡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
ትግርኛ እና ፍልስፈፍና ከተቋረጡት ፕሮግራሞች መካከል መሆናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ያብራሩት የዩኒቨርሲቲው የኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሐላፊ ዶር. ሳምሶን መኮንን፣ ለፕሮግራሞቹ መቋረጥ ዋናው ምክንያት፣ የሚማር ተማሪ መጥፋቱ ነው ብለዋል፡፡