የኦፌኮና የመአሕድ ድጋፍ ሰጭዎች ስምምነት

AAPO/OFC

ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና የመላ አማራ ሕዝብ ድርጅት ዓለምአቀፍ ድጋፍ ሰጭዎች በጋራ ለመሥራት ተስማምተው የመግባቢያ ሰነድ ቅዳሜ፣ ጥር 12/2010 ዓ.ም ከዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ በሚገኘው ማርክ ሴንተር ሂልተን ሆቴል ውስጥ ይፈራረማሉ።

ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና የመላ አማራ ሕዝብ ድርጅት ዓለምአቀፍ ድጋፍ ሰጭዎች በጋራ ለመሥራት ተስማምተው የመግባቢያ ሰነድ ቅዳሜ፣ ጥር 12/2010 ዓ.ም ከዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ በሚገኘው ማርክ ሴንተር ሂልተን ሆቴል ውስጥ ይፈራረማሉ።

የኦፌኮ ዓለምአቀፍ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ነጌሣ ኦዶ ዱቤና የመአሕድ ዓለምአቀፍ ድጋፍ ሰጭ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ መንግሥቱ አስፋው ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሁለቱም አሜሪካ፣ አውሮፓና አውስትራሊያ ውስጥ ሰፊ ድጋፍ ያላቸው መሆናቸውን ጠቁመው የሚሰጧቸው ድጋፎች የአድቮኬሲ፣ የገንዘብና የዲፕሎማሲ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ወደፊትም ሌሎችንም ወገኖች የሚወክሉ ድጋፍ ሰጭዎችን እንዲሁ የማስተባበር ሃሣብ እንዳላቸው አመልክተዋል።

ለሙሉው ቃለ ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኦፌኮና የመአሕድ ድጋፍ ሰጭዎች ስምምነት