ወጣቶችና የሰላም ግንባታ ተሳትፎ

Your browser doesn’t support HTML5

ወጣቶችና የሰላም ግንባታ ተሳትፎ

በድጋሚ የታደሰ በኢትዮጵያ የሚካሄዱት ጦርነቶችና ግጭቶች ወጣቶችን የበለጠ ተጎጅ እያደረጋቸው ነው ሲሉ በተለያዩ የአካባቢዎች የሚኖሩ ወጣቶች ይናገራሉ፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ከትግራይ፣ አማራ ና ኦሮምያ ክልሎች ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎች “የወጣቱን ህልም ያጨለሙ” ናቸው ያሏቸው ከዚህ በፊት የተካሄዱና አሁንም የቀጠሉ ግጭቶች እንዲቆሙና በድህረ ጦርነት የሰላም ግንባታ ጥረቶችም ተሳታፊ ሊደረግ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

በዚህ ዘገባ ዙርያ የአሜሪካ ድምጽ የሰላም ሚንስቴር ሃላፊዎችን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡