የግብጽ የመጨረሻው ስርወ መንግሥት ቅርሶች ተገኙ

  • ቪኦኤ ዜና
የመጨረሻው የግብጽ ስርወ መንግሥት ነገሥታት ቅርሶች 63 በሚደርሱ መቃብሮች ውስጥ መገኘታቸው ተነገረ፡፡

የመጨረሻው የግብጽ ስርወ መንግሥት ነገሥታት ቅርሶች 63 በሚደርሱ መቃብሮች ውስጥ መገኘታቸው ተነገረ፡፡

የመጨረሻው የግብጽ ስርወ መንግሥት ነገሥታት ቅርሶች 63 በሚደርሱ መቃብሮች ውስጥ መገኘታቸው ተነገረ፡፡

ባለሙያዎቹ በናይል ዴልታ ውስጥ በሚገኙ መቃብሮች ውስጥ ተገኝተዋል የተባሉትን ቅርሶችን ለማደስ እና ለመለየት እየሰሩ መሆኑን የሀገሪቱ የቅርስ ባለስልጣን ባለፈው ሰኞ አስታውቋል።

ቅርሶቹ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ305 ዓመተ ዓለም ጀምሮ ግብፅን ለ300 ዓመታት ያህል ገዝተዋል የሚባሉት የታላሜይክ ስርወ መንግሥት መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

ከቅርሶቹ መካከል የወርቅ ቁርጥራጮች እና ጌጣጌጦች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

የተወሰኑት ቅርሶች በአንደኛው የሀገሪቱ ሙዚየም ሊታዩ እንደሚችሉ የቱሪዝም እና ጥንታዊ ቅርሶች ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔቪን አል አሪፍ ተናግረዋል።

ባለሥልጣናት የግብፅ የአርኪኦሎጂዎስቶች ዴሚታ በተባለው ግዛትና ከተማ በቴል አል-ዲር ኔክሮፖሊስ በጭቃ ጡብ የተሠሩ መቃብሮችን ማግኘታቸውን ባለፈው ወር በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

በመቃብሮቹ አካባቢ የተገኙት ሌሎች ቅርሶች ከታላሜይክ ዘመን ጀምሮ ሃውልቶች፣ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ማስፈጸሚያዎች፣ የሸክላ ዕቃዎችና 38 የነሐስ ሳንቲሞች ይገኙበታል።

የታላሜይክ ሥርወ መንግሥት ወደ ሮም ግዛት አካልነት ከመቀየሩ በፊት የግብፅ የመጨረሻው ግዛት እንደነበር ተመልክቷል፡፡

በ305 ዓመተ ዓለም የተመሰረተው ሥርወ መንግሥት ያበቃው የመቄዶንያው ታላቁ እስክንድር ግብፅን በ332 ዓ.ዓለም ከያዘ በኋላ በንግሥት ኪሎፓትራ የመጨረሻው ዘመን ነው፡፡

እኤአ በ2018 በካይሮ በሚገኘው የግብፅ ሙዚየም ለመጀመሪያ ጊዜ ከታላሜይክ ዘመን የተገኙ ወደ 300 የሚጠጉ ቅርሶች ለዕይታ ቀርበዋል።