የ15 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሔማን በቀለ፣ የታይም መጽሔት የዓመቱ ድንቅ ልጅ ወይንም ‘Kid of the Year’ ተብሎ ተመርጧል።
በአሜሪካ፣ ፌርፋክስ ቨርጂኒያ ግዛት ውስጥ ኗሪ የሆነው ሔማን የቆዳ ካንሰርን ለማከም የሚያገለግል በአነስተኛ ዋጋ የሚገኝ ሳሙና ፈጣሪ ነው። የሔመን ግኝት በተለይ በድህነት ውስጥ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የቆዳ ካንሰር ህክምናን ተደራሽ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
Your browser doesn’t support HTML5
ታይም መጽሔት ሔመንን የመረጠው ወደፊት ሜላኖማ የሚባለውን ጨምሮ የቆዳ ካንሰርን የሚያክም መድሃኒት በአዲስ እና የበለጠ ተደራሽ በሆነ መንገድ ለማድረስ የሚያስችል ሳሙና በመስራቱ መሆኑን አስታውቋል።
ገና የ4 ዓመት ልጅ እያለ ከወላጆቹ ጋር ወደ አሜሪካ የመጣው ሔመን፣ ባለፈው ዓመት ኅዳር ወር ላይ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ሰዎች ሳሙናውን በቀላሉ ማግኘት ይችሉ ዘንድ ድርጅት ማቋቋም እንደሚፈልግ ተናግሯል።