የሩሲያ ጦር ኻርኪቭ ላይ ድብደባ መፈፀሙን ባለሥልጣናት ገለፁ

የሩሲያ ጦር ኻርኪቭ ላይ ባደረሰው ጥቃት የተጎዳው ህንፃ

የሩሲያ ጦር ኻርኪቭ ላይ ባደረሰው ጥቃት የተጎዳው ህንፃ

ሩሲያ በዩክሬን ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ኻርኪቭ ላይ ዛሬ ሰኞ ማለዳ የአየር ጥቃት ማደረሷንና አንድ ትምህርት ቤትና አንድ የመኖሪያ ህንፃ ማውደሟን የዩክሬን ባለሥልጣኖች ገለፁ።

በጥቃቱ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች ሃያ ስምንት ሰዎች መቁሰላቸውን ባለሥልጣናቱ አክለው አመልክተዋል።

አንደኛው ሚሳይል የወደቀው መጋዘኖች በሚገኙበት ሥፍራ መሆኑን የኻርኪቭ ከንቲባ ገልፀው “ሲቪሎች ላይ የተነጣጠረ የለየለት የሽብርተኛ አድራጎት” ብለውታል።

ከትናንት በስተያ ቅዳሜም ምሥራቅ ዩክሬን በምትገኘው ቻሲቭ ያር ከተማ ውስጥ በሩሲያ የሮኬት ጥቃት ከተመታ የመኖሪያ ህንፃ ፍርስራሽ ሥር በህይወት የተረፉ ሰዎችን ፍለጋ እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጿል።

በዚያ ጥቃት በያንስ አስራ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ተነግሯል።