የኮቪድ ክትባት ዘመቻ በዩጋንዳ

  • ቪኦኤ ዜና

ዩጋንዳ የኮቪድ ክትባት ከህንድ መንግሥት በስጦታ አገኘች።

ዩጋንዳ ነገ ረቡዕ ሃገር አቀፍ የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ እንደምትጀምር አስታወቀች።

ከህንድ መንግሥት በስጦታ ተጨማሪ አንድ መቶ ሺህ ክትባቶችን ከሁለት ቀናት በፊት ያገኘች ሲሆን በስጦታ ያገኘችው ክትባት ዘጠኝ መቶ ስድሳ አራት ሺህ ደርሶላታል።

የጤና ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው ቅድሚያ የጤና ሰራተኞች በመቀጠልም መምህራን፣ አረጋውያንን ጨመሮ ለቫይረሱ ይበልጥ ተገላጭ የሆኑ ሰዎች ይከተባሉ።

የዓለማቀፉን ወረርሽኝ ይዞታ በሚከታተለው ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ማዕከል መሰረት ዩጋንዳ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ 40,500፣ ያገገሙ 15,065፣ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 334 መሆናቸው ጠቁሟል።