የፍልሰተኞች ጀልባ ሰጥሞ 39 ሰዎች ሞቱ

  • ቪኦኤ ዜና

ከቱኒዚያ በሁለት ጀልባዎች ተሳፍረው ሜዴትራኒያን ባህርን ለማቋረጥ ከሞከሩ ስደተኞች መካከል ጀልባዎቹ ሰጥመው ቢያንስ ሠላሳ ዘጠኙ መሞታቸው ተዘገበ።

ባህሩን አቋርጠው ጣሊያን ላምፔዱሳ ደሴት ለመድረስ ከተሳፈሩት መካከል አንድ መቶ ስድሳ አምስቱን ስደተኞች የቱኒዥያ የጠረፍ ጥበቃ ሃይሎች ደርሰው እንዳወጧቸው የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።