በትግራይ በጦርነቱ የተስተጓጎለው ትምህርት ሚያዝያ 23 ይጀመራል

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ በጦርነቱ የተስተጓጎለው ትምህርት ሚያዝያ 23 ይጀመራል

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት፣ በትግራይ፣ ከሦስት ዓመት በላይ ተስተጓጉሎ የቆየው ትምህርት፣ ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደሚጀመር የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሓላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ፣ በክልሉ ከሦስት ዓመት በላይ ተዘግተው የቆዩ ትምህርት ቤቶች ተከፍተው፣ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስጀመር፣ መሰናዶው እየተጠናቀቀ ስለመኾኑ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎችም፣ ከትምህርት ርቀው ያሳለፏቸውን ዓመታት ለማካካስ፣ በአንድ ዓመት የሁለት መንፈቅ ዓመት ትምህርት በመሸፈን ለማስተማር ታቅዷል፤ ሲሉ፣ በምን ያህል ጫና እንደሚፈጸም አመልክተዋል፡፡

የተማሪዎችንና የመምህራንን አስተያየት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።