የትግራይ ክልል ትምህርት ቤቶችን ከተተኳሾች የማጽዳት ሥራ እየተከናወነ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራይ ክልል ትምህርት ቤቶችን ከተተኳሾች የማጽዳት ሥራ እየተከናወነ ነው

በትግራይ ክልል፣ ጦርነቱን ተከትሎ በትምህርት ቤቶች የተቀበሩና የተጣሉ ተተኳሾችን የማጽዳት ሥራ እየተከናወነ መኾኑን፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ፣ እስካለፈው ሳምንት ድረስ፣ በ1ሺሕ544 ትምህርት ቤቶች ቅጽር ውስጥ በተካሔደ ፍተሻ፣ 1ሺሕ230 ተተኳሾች ተቀብረው እና ተጥለው መገኘታቸውን፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

የቢሮ ሓላፊው፣ ከትምህርት ቤቶቹ ቅጽረ ግቢ ውጪ በብዛት ሊኖሩ እንደሚችሉ በመረዳት፣ ማኅበረሰቡ ተገቢ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡