የሶማሊያ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በድጋሚ ተመረጡ

ፎቶ ፋይል፦ ሞቃዲሾ

ፎቶ ፋይል፦ ሞቃዲሾ

አብዲ ሃሺ አብዱላሂ ትናንት በተካሄደው ድምፅ አሰጣጥ ሃያ ስምንት ድምጽ ያገኙ ሲሆን ዋናው ተፎካካሪያቸው ሃያ አራት ድምፅ አግኘተዋል።

ሃምሳ አራት መቀመጫ ያለው የላይኛው ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ምርጫ መጠናቀቁ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሀገሪቱን የሚመሩዋትን ፕሬዚዳንት የመምረጡን ሂደት ቀረብ አድርጎታል።

ፕሬዚዳንቱን የሚወስነው ጠቅላላ ምርጫ የሚከናወነው በሀገሪቱ ትልቅ ሥልጣን እና ተደማጭነት ያለው የታችኛው ወይም የመመሪያው ምክር ቤት አፈ ጉባኤውን ከመረጠ በኃላ ይሆናል።

ሁለት መቶ ሰባ አምስት አባላት ያሉት ምክር ቤትም ዛሬ አፈ ጉባኤውን ሊመርጥ ዕቅድ መያዙን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።