በሶማሌ ክልል ከብቶች በድርቅ እየሞቱ ነው

ፎቶ ፋይል፦ ጅግጅጋ

በሶማሌ ክልል የቦረና አጎራባች በሆነው የዳዋ ዞን በተከሰተው ድርቅ 25 ሺሕ የሚደርሱ የቁም እንስሳት መሞታቸውን ክልሉ አስታወቀ።

የሶማሌ ክልል አደጋ መከላከልናዝግጁነትቢሮ በድርቁ ምክንያት ተጎጂ የሆኑ ከ83 ሺ በላይ የሚሆኑ የዞኑ ነዋሪዎችም ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል።

ክልሉ ለዞኑ የንጹህ መጠጥ ውሃ በመኪና እያቀረበ መሆኑን እና የእንስሳት መኖም ከጅግጅጋና ጎዴ መኪኖች ተዘጋጅተው መጓጓዝ መጀመራቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሳዲቅ አብዱቃድር ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በሶማሌ ክልል ከብቶች በድርቅ እየሞቱ ነው