ዋይት ኃውስ ሩሲያ የኪሚካል የጦር መሳሪያዎችን በዩክሬን ላይ ልትጠቀም ትችላለች ሲል አስጠነቀቀ

የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ

የፕሬዘዳንት ባይደን አስተዳደር ሩሲያ የስነ ሕይወት(ባይሎጂካል) መሳሪያዎች ልትጠቀም ትችላለች ሲል ይፋ አደረገ፡፡ ይህ መግለጫ የወጣው ሩሲያ ሕገወጥ የኬሚካል መሳሪያዎች በዩክሬን እየተዘጋጁ ነው ማለቷን ዋይት ኋውስ ካጣጣለ በኋላ ነው፡፡

በዚህ ሳምንት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ዩክሬን የኬሚካል እና የስነ ሕይወት መሳሪያዎችን በዩናይትድ ስቴትስ እርዳታ እያዘጋጀች ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ “አስመሳይ” ሲሉ ሩሲያ እራሷ የስነ ሕይወት መሳሪያን በመጠቀም በዩክሬን ላይ የጅምላ ጥቃት ለመፈጸም መሰረት እየጣለች ይሆናል ብለዋል፡፡