የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኦሮምያ ክልል የሚገኙ ቅርንጫፎቹ መታሸጋቸውን እና 58 ሠራተኞቹ መታሰራቸውን አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኦሮምያ ክልል የሚገኙ ቅርንጫፎቹ መታሸጋቸውን እና 58 ሠራተኞቹ መታሰራቸውን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኦሮምያ ክልል የሚገኙት ሰባት ቅርንጫፎች በሙሉ በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች መታሸጋቸውን እና 58 ሠራተኞቹ መታሰራቸውን አስታወቀ።

ቅርንጫፎቹ የተዘጉበት እና በቅርንጫፎቹ የሚሠሩት ሠራተኞች የታሰሩበት ምክንያት እንዳልተገለጸ፣ ጉዳዩን በተመለከተ ለአሜሪካ ድምጽ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ነጻነት ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡ ምርት ገበያው ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ቢያሳውቅም ምላሽ እንዳልተሰጠውም ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ከኦሮምያ ክልል ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

የኬኔዲ አባተ ዘገባን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።