የናይጄሪያ ወታደሮች የቦኮ ሃራምን ከፍተኛ አባል ያዝን አሉ

  • ቪኦኤ ዜና

የናይጄሪያ ወታደሮች በጽንፈኛው የቦካሃራም ቡድን ውስጥ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለውን አባል መያዘቸውን ትናንት ዓርብ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

የቦኮ ሀራም አባሉ የተያዙት ለ12 ዓመታት ለአመጽ ማ እከል አድርገው ይንቀሳቀሱበት በነበረበት በሰሜናዊ ናይጄሪያ ቦርኖ ክፍለ ግዛት ውስጥ መሆኑንም የናይጄሪያ ወታደራዊ ቃለ አቀባይ ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ጨምረው እንደገለጹት ቡድኑ ተቀጣጣይ መሳሪያዎችን ለመስራት ይጠቀምባቸው የነበሩ ሁለት ስፍራዎችም በተደረገው ድንግተኛ ወረራ መያዛቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቡድኑ አባላት በተደረገባቸው ጥቃት እጃቸውን እየሰጡ ሲሆን እስካሁን ወደ 6ሺ የሚደርሱ የቡድኑ አባላትም መማረካቸው ተመልክቷል፡፡