የቀድሞ የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር አረፉ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሱሚይሉ ቡቤዬ ሜጋ በአውሮፓ ህብረት ስብሰባ ላይ ብራስልስ እአአ ሰኔ 28/2018

ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሱሚይሉ ቡቤዬ ሜጋ በአውሮፓ ህብረት ስብሰባ ላይ ብራስልስ እአአ ሰኔ 28/2018

የቀድሞ የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሱሚይሉ ቡቤዬ ሜጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ዛሬ አስታወቁ፡፡ የጤንነታቸው ሁኔታ ባላፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በአደገኛ ሁኔታ መታወኩን የገለጹት ሀኮሚችና ቤተሰቦቻቸው ሜጋ የሞቱት በማሊ ዋና ከተማ ባምኮ ውስጥ በነበረ አንድ ክሊኒክ ውስጥ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሜጋ ህክምና እንዲያገኙ ብዙ ጥያቄዎች የቀረቡ ቢሆንም አገሪቱን በሚመራው ወታደራዊ ጁንታ መከልከላቸው ተገልጿል፡፡

በማሊና እና በአካባቢው በሚገኙ የሳህል አካባቢዎች ከፍተኛ ተጽ እኖ የነበራቸው ሜጋ እኤአ በነሀሴ 2021 በአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር በሙስና ተከሰው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል፡፡

ሜጋ በሥልጣን ዘመናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነትና የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ኃላፊነትን ጨምሮ በፖለቲካው መስክ በበርካታ ኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ መሆኑን ተመልክቷል፡፡