ማሊ የፈረንሳይን አምባሳደር በ72 ሰዓት አገር ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፦አምባሳደር ጆኤል ሜር

ፎቶ ፋይል፦አምባሳደር ጆኤል ሜር

ማሊ የፈረንሳይ መንግሥት ስለማሊ የሽግግር መንግሥት “የጥላቻና የሚያስቆጣ” አስተያየት ሰጥቷል በሚል በአገሯ የሚገኙ የፈረንሳይ አምባሳደርን ከአገር እንዲባበረሩ መወሰኗን ትናንት ሰኞ አስታወቀች፡፡

ማሊ ስለ ቀድሞ የቅኝ ገዥዋ አገር ፈረንሳይ አምባሳደር ጆኤል ሜር በ72 ሰዓት ውስጥ አገር ለቀው እንዲወጡ ማበረሯን ያስታወቀችው ትናንት በአገሪቱ ቴሌቪዥን በተሰጠ መግለጫ ነው፡፡

መግለጫው የፈረንሳይ የአውሮፓና የውጭ ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ እንዲሁም የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ስለ ማሊ ባለሥልጣናት የሰጡት አስተያየት በጥላቻና በሚያስቆጣ አስተያየት የተሞላ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጄን የቭስ ለ ድሬን ፣ ባለፈው ሳምንት በሰጡት አስተያየት “የማሊ ወታደራዊ ጁንታ ህገ ወጥ እና ኃላፊነት የጎደላቸውን እርምጃዎችን የሚወስድ ፣ ከቁጥጥር ውጭ የወጣ ነው” ሲሉ መናገራቸው ተመልክቷል፡፡