ፍልሰተኞችን የያዘ ጀልባ ሰጥሞ 71 ሞቱ

የእርዳታ ሰራተኞች

ከሊባኖስ የተነሳ ፍልሰተኞችን የያዘ ጀልባ በሶሪያ ባህር ዳርቻ ሰጥሞ ቢያንስ 71 የሚሆኑ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የሊባኖስ መገናኛ ሚኒስትር አስታውቀዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ከተጫናት ሌባኖስ ወደ አውሮፓ ለመሄድ በሚደረግ የተስፋ መቁረጥ ጉዞ፣ በደንብ ባልተገነባና ከመጠን በላይ በትጫነ ጀልባ ላይ ለመሳፈር ሰዎች እየደፈሩ ነው።

የሶሪያ መገናኛ ሚኒስቴር ከአደጋው ከተረፉት አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት፣ ወደ አውሮፓ ለማቅናት ከሌባኖስ የተነሳችው ጀልባ ከ120 እስከ 150 ሰዎች ይዛ ነበር።

በአደጋው የቤተሰብ አባላቸውን ያጡ ሰዎች ሶሪያ ድንበር ላይ አስከሬን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

የሊባኖስ የመገናኛ ሚኒስትር አሊ ሃምዬ እንዳሉት፣ ከአደጋው የተረፉ 20 የሚሆኑት በሶሪይ ሆስፒታሎች ሕክምና በማግኘት ላይ ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ሶሪያውያን ናቸው። በሊባኖስ 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ሶሪያውያን ጦርነትን ሸሽተው በጥገኝነት ይኖራሉ።

ሊባንኖስን ያጋጥማት የኦኮኖሚ ድቀት በዓለም ከተመዘገቡትና ከባድ ከሚባሉት አንዱ ሲሆን፣ 6.5 ሚሊዮን የሚሆነው ሕዝቧ በድህነት ተመቷል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ፍልሰተኛችን የያዙ ሁለት ጀልባዎች የድረሱልን ጥሪ በማሰማታቸው፣ የሳይፕረስ የአደጋ ሠራተኞች በድምሩ 477 የሚሆኑ ተጓዡችን ከሞት ታድገዋል።

የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ እንደሚለው ባለፉት ሁለት ዓመታት ሊባኖስን ለቀው የሚወጡ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል። ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር፣ በዚህ ዓመት 70 በመቶ ጨምሯል።