ጋና ከዩክሬን የመጡ የመጀመሪያ ዙር ዜጎቿን ተቀበለች

  • ቪኦኤ ዜና

ዩክሬን የነበሩ አፍሪካውያን ተማሪዎች ፖላንድ ውስጥ በሚገኝ ጊዜያዊ መጠለያ እአአ የካቲት 28/2022

ጋና ሩሲያ ዩክሬንን በወረረችበት ሠዓት በዩክሬን በትምህርት ላይ የነበሩ ጋናዊያን ተማሪዎች የመጀመሪያ ቡድን ተቀበለች፡፡ የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ500 በላይ የሚሆኑ ጋናዊያን ተማሪዎች ከዩክሬን መሰደዳቸውን አስታውቀው ፍላጎታቸው ከሆነ ወደ ሃገራቸው መመለስ ይችላሉ ብለዋል፡፡

17 ተማሪዎችን የያዘው የመጀምሪያው ዙር ተመላሾች በሁለት ዙር በረራዎች ወደ ዋና ከተማዋ አክራ መመምለሳቸው የተገለጸ ሲሆን የሃገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊና የክልላዊ የውህደት ቢሮ ኃላፊ በሆኑት በክዋኩ አምፕራቴውም አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ከተማሪዎቹ መሃከል አንዷ የሆነችው ባኬዬ አግዬማንግ “መጥፎ አጋጣሚ በመሆኑ ወደ ሃገራችን ተመልሰናል፡፡ ቤተሰቦቻችን እና ጓደኞቻችን ሊረጋጉ ይገባል፡፡ መንግሥት እኛ እንድንመለስ የተቻለውን እያደረገ ነው” ያለች ሲሆን ለመመለሳቸው ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናዋን አቅባለች፡፡

ተማሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኙ ሲሆን 500 የሚሆኑ ጋናዊያን ተማሪዎች ሩሲያ ዩክሬንን በወረረችበት ሰዓት ወደ ጎረቤት ሃገራት ሮማኒያ እና ፖላንድ መሸሻቸው ተገልጿል፡፡