ጀርመን ከሩሲያ ልትነጋገር ነው ትናንሾቹ የአውሮፓ አገሮች ሰግተዋል

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ የጀመርን ቻንሰር ኦላፍ ስኮልዝ

የጀመርን ቻንሰር ኦላፍ ስኮልዝ ከሞስኮ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑትን ጋር በዚህ ወር መገባዳጃ ላይ ፊት ለፊት ተገናኝተው ሊወያዩ አስበዋል፡፡

አንዳንድ የጀርመን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ክወዲሁ በዚህ ወር ውስጥ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር ተገናኘተው በሩሲያና በዩክሬን ሳቢያ በአካባቢው በተፈጠረው ውጥረት ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

ይሁን እንጂ የጀርመኑ መሪ ከሩሲያ ጋር የሚፈልጉት አዲስ ግንኙነት በኃይል አቀርቦት ፖለቲካ እና በዩክሬን ጉዳይ ላይ በመነጋገር ለመጀመር ማሰባቸውን የጀርመን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስየሩሲያ ከፍተኛ ባለሥልጣናትም ጥር 1 እና 2 2014 ዓ.ም ሩሲያ በዩክሬይን ድንበር አቅራቢያ ስለገነባቸው ስላሰፈረችው ከ100ሺ በላይ ጦር እንደሚነጋገሩ ተመልክቷል፡፡

የምዕራባውያን አገሮች ባለሥልጣናት ኔቶ ወደ ሩሲያ አቅጣጫ ወይም ወደ ምስራቅ አውሮፓ የሚያደርገውን መስፋፋት ያቁም ስትል ሩሲያ የምታስቀምጠውን ቅደም ሁኔታ ለድርድር እንደማያቀርቡት ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ትላልቆቹ የአውሮፓውያን አገሮች ከሩሲያ ጋር በሚያደርጉት የተናጠል ስምምነት ደስተኛ ያልሆኑት ትናናሽ የአውሮፓ አገራት ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ድርድር እነሱም እንዲካተቱ እየጠየቁ ነው፡፡

የፊንላንድ ፕሬዚዳንት ሁሉምየአውሮፓ አባል አገራት መደበኛ የኔቶ አባል ይሁኑም አይሁኑ ዩናይትድ ስቴትስና ኔቶ ከሩሲያ ጋር በሚያደርጉት የደህንነት ጉዳይ ድርድር ላይ መካፈል አለባቸው ብለዋል፡፡

የጀመርኑቻንሰርልም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ጨምሮ ከአገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሩሲያ በባህር ውስጥ አድርጋ ወደ ጀርመን ለማስተላለፍ ያሰበቸውን የተፈጥሮ ጋዝ መስመር ስምምነት እንዳያጸድቁት ግፊት እያሳደሩባቸው ነው፡፡

የመመካከለኛውና የምስራቅ አውሮፓ አገሮችም የቀድሞዋን የጀርመን ቻንስለር ሩሲያና ጀርመንን ለማገናኘት ላሰበው ይህን የጋዝ መስመር እንዳያጽድቁ ሲወትውቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

የጣሊያኑጠቅላይ ሚኒስትር ማሮዮ ድራጊ ሩሲያ ዲፕሎማሲ ድል ለመቀዳጀት የምታደርገው ማስፈራራት እንጂ ዩክሬንን አትወርም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

በሩሲያ ጉዳይ ላይ በምዕራባውያን መካከል መፈጠሩ ሲገልጽ፣ ትናንሾቹ የአውሮፓ አገሮች ትላልቆቹ የአውሮፖ አገሮች ከሩሲያ ጋር በሚያደርጉት ድርድር አሳልፈው ይሰጡናል የሚል ስጋት ያላቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡