ኢትዮጵያ ውስጥ የቀሩት ዝሆኖች 1900 ብቻ ናቸው

አሜሪካዊው ጋዜጠኛና ፊልም ሰሪ አንቷን ሊንድሌይ

በኢትዮጵያ ውስጥ ህገ ወጥ አደን እየተባባሰ ሄዶ፣ በርካታ የዱር እንስሳት እየተገደሉአካላቸው በከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሸጥና የሚገኘው ገንዘብ ከግል ጥቅም አልፎ ለጦር መሳሪያ ግዢና እርስ በርስ ግጭቶችን ማባባሻ እየዋለ እንደሚገኝ በተለያየ ጊዜ ይገለፃል። የኢትዮጵያ የዱርእንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ያሰራውና አርብ እለት ለእይታ የቀረበው

'Ethiopia’s Elephant crisis' የተሰኘ የኢትዮጵያ ዝሆኖች ያሉበትን አስጊ ሁኔታ ላይ የሚያሳይ ጥናታዊ ፊልም እንዳረጋገጠውም ሀገሪቱ ከ1980ዎቹ አንስቶ 90 በመቶ የሚሆኑ ዝሆኖቿን አጥታ፣ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ዝሆኖች 1900 ብቻ ናቸው። በዚህ 40 ደቂቃ የሚፈጀውና በአምስት የተለያዩ ብሄራዊ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ ዝሆኖች ይዞታን የሚያስቃኘው ጥናታዊ ፊልም ዋና አዘጋጅና ዳይሬክተር አሜሪካዊው ጋዜጠኛና ፊልም ሰሪ አንቷን ሊንድሌይ አነጋግረናቸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ውስጥ የቀሩት ዝሆኖች 1900 ብቻ ናቸው