ኒው ዮርክ —
ከኮሮናቫይረስ ሥጋት ጋር በተያያዘ በሳዑዲ አረቢያ እሥር ቤቶች ውስጥ በአንድ ላይ ተፋፍገው የተቀመጡ ኢትዮጵያዊያን የሚገኙበት ሁኔታ አስከፊ መሆኑን ገልፀው ወደ ሃገራቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። በሳዑዲ አረቢያና በየመን ድንበር አካባቢ የሚገኘውና “ጄዛን” ተብሎ የሚጠራው እሥር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ በስልክ የገለፁልን ስደተኞች፤ ከስድስት ወራት በፊት “ወደ ሀገራችሁ እንድትመለሱ ከመንግሥታችሁ ጋር ተነጋግረናል” በማለት የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ወታደሮች ወደ እሥር ቤቶቹ እንዳስገቧቸው ይገልፃሉ።
ነገር ግን ከዚያ ወዲህ ማንም እንዳልተመለከታቸው፣ በቂ ምግብ እንደማያገኙና የሚገኙበት የእስር ቤቱ ክፍል ጠባብ በመሆኑ ከሚፈጠር መተፋፈን እና ሙቀት የተነሳ ለሕመም እየተዳረጉ መሆኑን ይናገራሉ።
ከወሎ አካባቢ ተነስቶ በየመን የባህር ጉዞ ሳዑዲ ለመድረስ 70 ሺህ ብር ያህል ማውጣቱን የሚናገረው አሁን በጄዛን እስር እንደሚገኝ ነው ወጣቱ የገለፀው። እስረኞቹ ስላሉበት ሁኔታ ከሚያስረዳበት ቃለ ምልልሱ ይጀምራል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5