በምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ጀመረ

በምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች አንዳንድ ከተሞችና ወረዳዎች ውስጥ ለሁለት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ከትናንት ጀምሮ መከፈቱን ከነዋሪዎች መካከል ገለፁ።

የኢትዮቴሌኮም ምዕራብ ቀጠና ዳይሬክተር አቶ ሙላቱ ጉደታ አገልግሎቱ በሁለቱም ዞኖች ከትናንት ጀምሮ መከፈቱን አረጋግጠዋል።

የኦሮምያ ኮሙኒኬሽንስ ቢሮ ሃላፊ ምክትል ሀላፊ አቶ ግዛቸው ገቢሳ "አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረው መንግሥት የህግ በላይነትን ለማረጋገጥ በወሰደው እርምጃና አንዳንድ ስፍራዎች ላይ መሰረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት ደርሶ ስለነበር ነው" ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በምዕራብና ቄለም ወለጋ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ጀመረ