ወቅታዊ ችግሮችን በንግግር ለመፍታት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አሳሰቡ

Your browser doesn’t support HTML5

ወቅታዊ ችግሮችን በንግግር ለመፍታት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አሳሰቡ

81ኛው የድል ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ ተከብሯል። በዝግጅቱ ላይ የተገኙት ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት ንግግር፣ የዛሬው ትውልድ ከቀደሙት አርበኞች ገድል በመማር ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት፣ የቀደምት ኢትዮጵያውያን አርበኞችን ገድል በማስታወስ ለዛሬው ትውልድ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አስተያየታቸውን የሰጡን የበዓሉ ታዳሚያንም፣ “ወጣቱ በአንድነት የመቆም ልምድን ከአርበኞች ታሪክ መቅሰም አለበት” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ