በትግራይ 2ነጥብ3 ሚሊዮን ሕፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ 2ነጥብ3 ሚሊዮን ሕፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም

በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሠተውን ግጭት ለማስቆም፣ በመንግሥት እና በህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት ቢፈረምም፣ አኹንም፣ “ከ2ነጥብ3 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም፤” ሲል፣ የሕፃናት አድን ድርጅት /ሴቭ ዘ ችልድረን/ አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ የኮሚዩኒኬሽን፣ የሚዲያ እና የአድቮኬሲ ሥራ ክፍል ሐላፊ ሕይወት እምሻው፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ፣ ከ3ነጥብ5 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት፣ ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቀለው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋራ በመተባበር፣ በክልሉ፣ በቅርቡ ትምህርት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው፤ ብሏል፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሓላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ በክልሉ፣ ወደ ትምህርት ቤት ለመግባት የሚጠባበቁ 2ነጥብ4 ሚሊዮን ተማሪዎች እንዳሉ ጠቅሰው፣ እነዚህን ሕፃናት በልዩ ልዩ መንገዶች ትምህርት ለማስጀመር በመሥራት ላይ ናቸው፡፡

ለዚህ ዕቅድ መሳካትም፣ የሚመለከታቸው አካላት ኹሁሉ፣ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሐላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።