በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በትምህርቱ ጎራ ያሳደረው ጫና

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በትምህርቱ ጎራ ያሳደረው ጫና

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፉት አስርተ ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማያውቅ ያለው አፍሪካ ቀንድን የመታው አስከፊ ድርቅ በኢትዮጵያ ብቻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሲያፈናቅል፣ ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ሕጻናት ከትምህርት ገበታቸው እንዲስተጓጎሉ እና በመቶዎች የሚቆጠሩት ትምህርት ቤቶች ደግሞ እንዲዘጉ ምክኒያት መሆኑ ተዘገበ።

ዓለም አቀፉ የረድኤት ድርጅት ሴቭ ዘ ችልድረን እርዳታ ቡድን፣ ያላቸውን ሁሉ ያጡ ወላጆች ከተጠለሉባችው የስደተኛ ካምፖች አቅራቢያ ሕጻናቱን በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚያሰባስቡ ማዕከሎችን ገንብቷል።

አርብቶ አደሮችን እና በግብርና የሚተዳደሩትን በተመሳሳይ የነበራቸውን መተዳደሪያ ባሳጣቸው ድርቅ ሳቢያ ከ900 ሺ በላይ አባወራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ለመፈናቀል ተገደዋል።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች በኢትዮጵያ በተለይም በገጠር እና ከከተሞች ራቅ ብለው በሚገኙ አካባቢዎች እጅግ ደካማ ናቸው።

እንደ የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ግምገማም ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት የመጀመሪያ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያሸጋግግራቸውን ውጤት አያመጡም።

በዚህም የተነሳ ከአጠቃላዩ 54 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ብቻ ናቸው ከስምንተኛ ክፍል የተሻገረ የትምሕርት ደረጃ የሚደርሱት።