የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የቫይረሱ ወረርሽኝ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ቫይረሱ በኢትዮያ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛው ዕለታዊ የተጠቂዎች ቁጥር ባለፈው ቅዳሜ መመዝገቡንም ያስታወሱት ሚኒስትሯ፣ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ ቢበዛ 3 ከመቶ ከነበረበት ወደ 12 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል፡፡ አሁን ላይ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት በተለያየ መጠን በመላ ሀገሪቱ የተዳረሰ ሲሆን በአዲስ አበባ ደግሞ እድሜው ከ35 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ነዋሪ ክትባቱን ማግኘት እንደሚችል ዶ/ር ሊያ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ባለፉት ሳምንታት ከወትሮው በላቀ መልኩ በመጨመር ላይ ነው፡፡ በተለይ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ ከ5 ሺህ 500 በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙበት ያለፈው ሳምንት ስርጭቱ በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡
በዚሁ ጉዳይ ላይ ዛሬ ነሐሴ 18 መግለጫ የሰጡት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት የተመዘገበው 1282 የኮቪድ 19 ተጠቂዎች ቁጥር ቫይረሱ በኢትዮያ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛው ዕለታዊ የተጠቂዎች ቁጥር መሆኑን ገልጸው፣ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ ቢበዛ 3 ከመቶ ከነበረበት ወደ 12 በመቶ ማደጉን አብራርተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5