ህወሓትና መንግሥት አዲስ ጥቃት በመክፈት እየተካሰሱ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ህወሓትና መንግሥት አዲስ ጥቃት በመክፈት እየተካሰሱ ነው

የኢትዮጵያ መንግሥት “ህወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ ከፍቷል” ሲል ክሥ ያሰማ ሲሆን ህወሓት ደግሞ “በተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃት የፈፀመው የፈዴራል መንግሥት ኃይል ነው” ብሏል።

በሌላ በኩል ትናንት እኩለ ሌሊት መቀሌ ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሙን የፈረንሳይ ዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) ዘግቧል።

ጦርነቱ ተባብሶ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት የሰላም ጥሪዎች የቀጠሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ግጭቱን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲቆምና ሰብዓዊ ድጋፎች እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።