አዲስ አበባ እና ባህር ዳር —
ህወሓት ትናንት ሌሊት ወደ ባህርዳር የተኮሳቸው ሮኬቶች ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሳቸውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጄር ጄነራል ይልማ መርዳሳ አስታወቁ። ሮኬቶቹ ከየት እንደተተኮሱ እናውቃለን ያሉት ዋና አዛዡ ያረፉትም በገበሬ ማሳ ላይ ነው ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
እንደ ሜጄር ጀነራሉ ገለፃ በህወሓት እጅ የነበሩ ሮኬቶች አየር ኃይሉ ከዚህ ቀደም ባካሄዳቸው ድብደባዎች ወድመዋል። ህወሓት አሁን የተኮሳቸውም በኮንትሮባንድ እና በተለያየ መንገድ ያስገባቸው እና በየጉድጓዱ የደበቃቸው ናቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል እየወሰዳቸው ባሉ እርምጃዎች ሲቪሎች ተጎድተው እንደማያውቁ የገለፁት ዋና አዛዡ ህወሓት በዚህ ረገድ የሰነዘራቸውን ውንጀላዎችም አጣጥለዋል።
Your browser doesn’t support HTML5
በሌላም በኩል ወደ ባህርዳር የተተኮሱት ሮኬቶች ጉዳት አለማድረሳቸውን እና ያረፉትም ማሳ ላይ መሆኑን የዓይን እማኞችም ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5